APRIL 20, 2024 | METRO-DC AREA | JOINT CONFERENCE
The fourth of the five regional celebrations was held in Landover, MD on Saturday April 20, 2024.
በጉዞ ኢዮቤልዩ መርሃግብር የቤተክርስቲያናት መሪዎችና መጋቢዎች ተሳትፎ ኣመርቂ መሆኑ ተነገረ።
ዋሺንግተን ዲሲ፣ በዚህ አመት በጁላይ ወር ውስጥ ለሚከበረው የኢ.አ.ክ.ህ. በሰሜን አሜሪካ የወርቅ ኢዮቤልዩ ታሪካዊ በዓል ዝግጅት ጉዞ ኢዮቤልዩ የተሰኘ መርሃግብር በተለያዩ ጊዜያት በልዩ ልዩ የአሜሪካ ግዛቶች በመካሄድ ላይ ይገኛል፥፥ እስካሁን ድረስ በሲንሲናቲ ከተማ የኢንዲያና፣ የከንታኪና የኦሃዮ ስቴቶች፡ በፍሪሞንት ከተማ የቤይኤሪያ አካባቢ፣ በካንሳስ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ፣ሜሪላንድና ቨርጅኒያ የሚገኙ አማኞች በላንዶቨር ከተማ በደመቀ ሆኔታ እንዳከበሩ ተገለጸ። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን መሪዎች መርሃግብሩን በኤፕሪል 18 ቀን በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት ከያሉበት የአለም ክፍል በዙም አክብረዋል።
በምስራቅ ዞን ወጌላዊያን አማኞች ከሶስት ሺህ በላይ ሰዎች በተገኙበት በኤፕሪል 20 የተከበረው የጉዞ ኢዮቤልዩ መርሃግብር አከባበር ብዙዎችን ያስገረመ ነበር። ጊዜው የእግዚአብሄር ቃል የተሰበከበት፤ በአካባቢው ካሉት የህብረት መዘምራን የተውጣጡ፣ እና ተጋባዥ የሶሎ ዘማሪዎች ዝማሬዎቻቸውን ያቀረቡበት ነበር።
ህብረቱ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተመሳሳይ የሆኑ ዝግጅቶች በአትላንታ፣ኖርዝ ካሮላይና፣ ላስቬጋስ፣ኦሬገን ቺካጎ፣ቴኔሲ፣ቦስተን እና ሚኒያፖሊስ ለማድረግ በየአካባቢው የሚገኙት አብያተክርስትያናት በብዙ መሰጠት በመትጋት ላይ ናቸው።
የህብረቱ ዋና ዳይረክተር ፓስተር ሰለሞን ጥላሁን እንደገለጹት እስከአሁን በተደረገውና እየተካሄደ ባለው ዝግጅት የቅዱሳንና የአካባቢ ቤተክርስቲያን መሪዎች በመቀራረብና ተከታታይ ስብሰባዎችን በማድረግ ጊዜአቸውንና ገንዘባቸውን ሳይሰስቱ በመስጠት እንዲሁም ዝግጅቱ በሚጠይቀው ነገር ሁሉ በፈቃደኝነት በመሳተፍ በክርስቲያናዊ ቤተሰብነት መንፈስ አከናውነዋል:: አክለውም የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር አስተባባሪዎችና የህብረቱ አመራር በተመለከቱት ነገር እጅግ መደሰታቸውንና በይበልጥ በአገልግሎታቸው በበለጠ ሁኔታ እንዲነሳሱ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
“ለነዚህ ጉዞ ወደ ኢዮቤልዩ ቅድመ በዓል ከበራዎች መሳካት በየከተማው ላሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች እጅግ የላቀ ምስጋናችንንና አድናቆታችንን ማስተላለፍ እንወዳለን። በመካከላችሁ ካየነው መተሳሰብና ፍቅር የተነሳ “ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ እናንተ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ፤ ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ ስለ ሰራችሁ ባሰብኋችሁ ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ” የሚለውን ሓዋሪያዊ ስሜት አሳድሮብናል።” በማለት ዳይሬክተሩ ጨምረው ገጸዋል።
በወርቅ ኢዮቤልዩ አከባበር መርሃግብር መሰረት በጁላይ 24 የብሄራዊ የጸሎት ቡድን ስብሰባ፣ በጁላይ 25 የዓለም አቀፍ የወንጌላዊያን መሪዎች ስብሰባ እንዲሁም ከጁላይ 26 እስከ ጁላይ 27 የታላቁ የወርቅ ኢዮቤልዩ ዋናው ከበራ ይከናወናሉ።
Regional Conferences
The five regional celebrations will be held across North America, including West Coast Zone, Central Zone, Heartland Zone, East Coast Zone and Southern Zone.