
LIVE STREAMING
እኛ ሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት፣ አምላካችን እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ባለቤት እርሱ ብቻ መሆኑን ያሳውቅ ዘንድ ቀድሞ በደነገገው ኢዮቤልዩ መርህ የሃምሳኛ ዓመታችንን ልዩ በሆነ መልኩ ልናከብር ቆርጠናል! ይህ ኢዮቤልዩ፣ ዋና ዋና የአንቀጹ ሐረጎች በእኛና በሩቅም በሚሰሙን ዘንድ ሁሉ፣ አንድ ካደረገን የክርስቶስ ፍቅር ጋር፣ እንዲገለጥ እናውጃለን! ለእያንዳንዱ ጥቅም፣ ለጋራ በረከት፣ ለእግዚአብሔር ክብር ኢዮቤልዩን እናክብር እንላለን! አዋጅ! አዋጅ! እናንት ወንጌላውያን ስሙ፣ ላልሰማው አሰሙ! እግዚአብሔር ቀድሞ በተናገረበት ቃሉ አሁንም ይናገራልና አድምጡ! ሳቡ ተሰብሰቡ የሰንበታት ሰንበትን ኢዮቤልዩን አስቡ! ታላቁን የጌታን ዓመት ለማክበር በየዞኑ ተሰብሰቡ! ጥንታዌ ጥንቱ፣ አልፋ ኦሜጋው ይጠራሃል፣ ለራስህ ስማ፣ ለቤትህ አሰማ፣ ለማህበሩ አሰማ፣ ኢዮቤልዩ የሰንበታት ሰንበት፣ የታላቅ ተሐድሶ ዋዜማ፣ ጥሪ እነሆ፣ ተጠርተሃል!